ethiotam3
Corona Virus Donations
ለሣክራሜንቶና አካባቢው ለምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ :
አቶ ሜንሺን ኮነሊ የሣክራሜንቶ ነዋሪ የሆኑ አሜሪካዊ ወገናችን ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ማኀበረሰብ ማዕከል ሆነው ቆይተዋል ። የአባልነት ግዴታቸውንም በየጊዜው እየተወጡ በምናዘጋጃቸው ዝግጅቶች ሁሉ ግምባር ቀደም በመሆን የሚያግዙን ዓለም አቀፍ መልካም ዜጋ ናቸው ።
ይኸው አሁንም ወገን በተቸገረ ወቅት ከጎናችን ተሰልፈው ዛሬም በኮረና ቫይረስ ሳቢያ ለሚደርሰው ችግር ለተጎጂዎች ይድረስ ብለው $1000.00 ( አንድ ሺህ ደላር ) ለማዕከላችን አበርክተዋል።
ውድ ወንድማችንን አቶ ሜንሺን ኮነሊ በሁላችንም ስም ከፍተኛ ምሥጋናችንን እናቀርብላቸዋለን ።
እግዚአብሔር ይስጥልን !
በሣክራሜንቶ የኢትዮጵያዊያን ማኀበረሰብ ማዕከል ቦርድ አስተዳደር