ethiotam3
የምወዳችሁ ኢትዮጵያውያ
///////////// ይህን ማስታወቂያ በማንበብ ምላሽ እንድትሰጡ እና ለሌሎችም እንድታደርሱ በትህትና ይጠየቃል /////////////
የምወዳችሁ ኢትዮጵያውያን
በማህበራዊ አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የሚኖረውን እና በአሜሪካን መንግስት የመረጃ አያያዝ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ ያለው የህዝብ ቆጠራ(Census) በየ10 አመቱ ይደረጋል። ይህ የህዝብ ቆጠራ በዚህም አመት በመካሄድ ላይ ሲሆን መስከረም ላይ ይጠናቀቃል።
የምንኖርበት አካባቢ (ካውንቲ/ስቴት) እንዲሁም እንደ ኢትዮጵያዊያንም ማህበረሰባችን በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ ግንባታ፣ የመንግስት ልዩ ልዩ ድጋፎችን በተመለከተ የህዝብ ብዛት ቁጥር በየአመቱ የሚመደበውን የፌደራል መንግስት የበጀት ድጋፍ የሚውስን ስለሆነ (ለምሳሌ በአንድ ልጅ 18ሺህ ዶላር መንግስት ይመድባል - ካልተመዘገብን ኮሚዩኒቲያችንን ይህንን ያጣል) - በአስር አመት አንዴ የሚደረግን የህዝብ ቆጠራ (Census) መሳተፍ ወሳኝ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆንን አሜሪካዊ ዜግነት ያለን ፎርሙን ስንሞላ በትውልድ ኢትዮጵያዊያን መሆናችንን በመጥቀስ የማህበረሰባችንን ትክክለኛውን ቁጥር ለማሳወቅ ስለሚረዳ የተቻለንን ጥረት እናድርግ።
እያንዳንዳችን የመኖሪያ ፍቃድ ቢኖረንም ባይኖረንም፣ የአሜሪካ ዜግነት ያለንም ሆነ በግሪን ካርድ የምንኖር፣ ከኢምግሬሽን ሁኔታ ጋር በምንም የማይገናኝ በመሆኑ በፓስታ ቤት የተላከልንን ፎርም ወይም በስልክ አልያም በኢንተርኔት ፎርም በመሙላት ሁላችንም የህዝብ ቆጠራው አካል እንድንሆን ጥሪ እናቀርባለን።
በOnline ለመሙላት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ -
https://my2020census.gov/
https://public.govdelivery.com/landing_pages/17020/7bcf8e141d08e1c2100473d7991c8d76